የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረውና በኮሚሽኑ አስተባባሪነት በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ ዛሬም ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ 01
ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረውና በኮሚሽኑ አስተባባሪነት በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ ዛሬም ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡ በዛሬው መርሃ-ግብር በጅግጅጋ ከተማ በሶማሌ ክልል ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አዳራሽ ውስጥ የፋፈን ዞን የተወካዮች መረጣ በመከናወን ላይ ሲሆን በሂደቱም የሃሮራይስ ወረዳ፣ የቀብሪበያህ ከተማ አስተዳደር፣ የቀብሪበያህ ወረዳ እና የጎልጃኖ ወረዳዎች ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በሌላ ከኩል በጎዴ ከተማ በጎዴ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ በትይይዩ በመደረግ ላይ የሚገኘው መርሐ-ግብር በሸበሌ ዞን የሚገኙትን የአሌ፣ አዳዲል፣ ቀላፎ እና ኢሜ በሪ ወረዳዎችን በማሳታፍ ላይ ይገኛል፡፡
በትናንቱ መርሃ-ግብር ላይ እንደተደረገው ሁሉ በዛሬው ዕለትም ለተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት እና ሰለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጓል፡፡ ገለፃውን ተከትሎም መድረኩ ለውይይት ክፍት የሆነ ሲሆን ተሳታፊዎችም ጥያቄዎችን በማንሳት የውይይቱ ተካፋይ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡
በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ 02