የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ነው፡፡

south et2

በዲላ እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የጌዴኦ ዞን እና የወላይታ ዞን የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዲላ ከተማ የጌዴኦ ባህል አዳራሽ እየተከናወነ የሚገኘው የጌዴኦ ዞን የተወካዮች መረጣ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን 1,300 የሚሆኑ ተሳታፊዎች 13 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በመወከል ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በወላይታ ሶዶ ከተማ ጉታራ የባህል አዳራሽ እየተከናወነ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ በወላይታ ዞን የሚገኙ 23 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በማሳተፍ ለአራት ቀናት ቆይቶ የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሂደቱም ወረዳዎቹን በመወከል 2,300 የሚደርሱ ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ እንደሚሰበሰቡ ይጠበቃል፡፡

በመድረኮቹ ተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡

 

south et