የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን አስመረጠ፡፡

somali dawa zone

በሞያሌ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ተቋም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከሙባረክ፣ ሞያሌ፣ ቀዳዱሞ እና ሁደት ወረዳዎች የተውጣጡ 400 የሚሆኑ ተሰብሳቢዎች ተሳትፈዋል፡፡

በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ መሰረት ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ተደርጓል፡፡