የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በይፋ ተጀመረ

111111 min

ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ሁለተኛው ምዕራፍ የሆነው የባለድርሻ አካላት ምክክር ዛሬ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ጨፌ ኦሮሚያ መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል፡፡ በዚህ መድረክ 320 የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ ከ1ሺ 700 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አካላት፣ የተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች […]

“በኦሮሚያ ክልል የምክክር ሂደት የህብረተሰቡ የመደማመጥና የመወያየት ፍላጎት የሚደነቅ ነው” – ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር)

ambaye and yonas

“በኦሮሚያ ክልል የምክክር ሂደት የህብረተሰቡ የመደማመጥና የመወያየት ፍላጎት የሚደነቅ ነው” – ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም ካለፈው ሰኞ ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህብረተሰብ ክፍሎች የምክክር መድረክ ተጠናቋል። የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ መጠናቀቁን አስመልክቶ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) እና ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። […]

የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊዎች የተወካዮች ምርጫ እያከናወኑ ነው።

webb min

ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ እየተደረገ ነው። በዛሬው ዕለት በቀጣይ የምክክር ሂደቶች የሚሳተፉ ተወካዮች ከአሥሩም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመረጡ ነው። የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ምርጫ በእያንዳንዱ የክላስተር ቡድን ደረጃ የሚከናወን ነው። እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል በክላስተር ደረጃ 8 ተወካዮችን በሚስጥራዊ መንገድ ይመርጣል። በአንድ ክላስተር […]

በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

4d7a9530 min

ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል የምክክር መድረክ የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች ትናንት ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም በአራት ክላስተር ተከፍለው የቡድን ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ አነስተኛ ቡድኖች በተናጥል አጀንዳቸውን ለይተው ካጠናቀቁ በኋላ አንድ ንዑስ ቡድን በመመስረት አጀንዳዎቻቸውን እያጠናቀሩ ነው። የክልል የህብረተሰብ ወኪሎች ምክክር 80 ንዑስ ቡድኖች ሲኖሩት እያንዳንዱ ክላስተር 20 ንዑስ ቡድን እንዲኖረው ተደርጎ ምክክሩ […]

በኦሮሚያ ክልል የወረዳ የማኅበረሰብ ክፍሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር እየተካሄደ ነው።

oromia 06

8/4/2017 በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ትናንት ጠዋት በይፋ በተከፈተው የምክክር መድረክ ከ356 የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ7000 በላይ የማኅበረሰብ ክፍል ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መርሐግብር ጀምረዋል። በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የማኅበረሰብ ክፍሎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ዕድሮች፣ መምህራን፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ራሳቸውን የማገልጹበት መተዳደሪያ ያላቸው፣ ተፈናቃዮች፣ በባህላቸውና በሙያቸው ምክንያት የተገለሉ፣ ነጋዴዎች እና የማኅበረሰብ መሪዎች ናቸው። ተሳታፊዎቹ በ4 […]

የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀመረ።

oromia agenda (3)

ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ዛሬ ጠዋት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) በኢትዮጵያ ያሉ የአለመግባባት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መመካከር አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ እጅግ መሠረታዊ የአለመግባባት መንስኤዎችን በአጀንዳ መልክ በማሰባሰብ ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም […]

የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ተከናወነ።

baledi

የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ተከናወነ። በኦሮሚያ ክልል ለሚከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ቀጥለዋል። በዛሬው ዕለትም በኦሮሚያ ክልል ተቋማትና ማኅበራትን ወክለው በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ላይ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጠበጫ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ባለድርሻ አካላቱ የሀገራዊ ምክክር ምንነት፣ አስፈላጊነትና ሂደትን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። ባለድርሻ አካላቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ […]

የሞደሬተሮች ሥልጠና ተከናወነ

mo1

የሞደሬተሮች ሥልጠና ተከናወነ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በሚቀጥለው ሳምንት ለሚጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የሞደሬተሮች ሥልጠና ተከናውኗል። ሞደሬተሮቹ በክልሉ ለሚከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ያላቸውን ሚና በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። 48 ሞደሬተሮች በተገኙበት በዚህ ሥልጠና ሞደሬተሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ተሳታፊዎችን በቡድን የማደራጀት፣ የሂደቱን ቅደምተ ተከተል ማሳለጥ፣ በጎ ፈቃደኞችን የማሰማራትና ኮሚሽኑ በክልሉ በሚያከናውናቸው ዝርዝር ቴክኒካዊ የምክክር ሂደደቶች ላይ […]

የአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች ጥሪ

aba

የአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች ጥሪ ታህሳስ 1/2017 አዳማ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ከታህሳስ 7/2017 ጀምሮ የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንዲሳካ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች ገለፁ። በጀስቲስ ፎር ኦል አስተባባሪነት በምክክሩ ዙሪያ ለሁለት ቀናት ባደረጉት ውይይት የኮሚሽኑን ስራ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል። የምክክሩ ተሳታፊዎች በምክክር መድረኩ ለመሳተፍ ዝግጅት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። Waamicha Abbootii Gadaa fi […]

#ኦሮሚያ ክልል

oromiya. preparatory design new

#ኦሮሚያ ክልል #ህዳር 30/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍን ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ መርሃ-ግብሩ ከታህሳስ 7 እስከ 15 ቀናት 2017 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ ይካሄዳል፡፡ በሂደቱም፦ 👉7020 የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች 👉356 ወረዳዎች 👉1700 የክልል ባለድርሻ አካላት 👉48 ሞደሬተሮች 👉356 የክልሉ ተባባሪ አካላት 👉150 በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ Komishiniin […]