በካናዳ የምክክር መድረክ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ገቢ ተደረጉ

በካናዳ የምክክር መድረክ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ገቢ ተደረጉ መስከረም 6/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በካናዳና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም በቶሮንቶ ከተማ አጀንዳ ማሰባሰቡ ይታወሳል፡፡ በዚህ መድረክ የተሰበሰቡ ባለ 66 ገፅ 11 የአጀንዳ ሰነዶችን የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ በኮሚሽኑ ዶክመንቴሽን መምሪያ በኩል ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ገቢ አድርገዋል፡፡ […]