የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአጀንዳ አሰባሰብ አሰራር ስርዓቱ የሚያግዙ ግብዓቶችን ከባለድርሻ አካላት ሰበሰበ፡፡

addis ababa 1.

ኮሚሽኑ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያካሂደው አጀንዳ የማሰብሰብ ተግባር ያዘጋጀውን ረቂቅ የአሰራር ስርዓት በሚመለከተታቸው ባለድርሻ አካላት አስተችቶ ግብዓቶችን ሰብስቧል፡፡ በአዲስ አበባ ሀይሌ ግራንድ ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ መርሐ-ግብር ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከ250 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም ከመንግስት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው […]

“የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡” ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ

addis ababa 2

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብና የሀገራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የግብአት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ማኅበራት፣ ተቋማትና የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወከሉ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ለውይይቱ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሂደቱ ላይ በንቃት […]