ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን አስመረጠ፡፡
በሞያሌ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ተቋም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከሙባረክ፣ ሞያሌ፣ ቀዳዱሞ እና ሁደት ወረዳዎች የተውጣጡ 400 የሚሆኑ ተሰብሳቢዎች ተሳትፈዋል፡፡ በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ መሰረት ተሳታፊዎች ለአጀንዳ […]