የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

“2018 ዓ.ም የምክክሩ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊተባበር ይገባል- ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ(ፕሮፌሰር)

prof web
“2018 ዓ.ም የምክክሩ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊተባበር ይገባል- ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ(ፕሮፌሰር)
ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫው ላይ ተገኝተው ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ(ፕሮፌሰር) ኮሚሽኑ በደቡብ አፍሪካ እና በአሜሪካ እና በካናዳ የተከናወኑ የሀገራዊ ምክክር መድረኮች በስኬት መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
ከዳያስፖራ ኢትዮጵያዊን ጋር የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ምክክር እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ በርካታ አጀንዳዎች መሰብሰባቸውን ተናግረዋል፡፡
ከአጀንዳ ማሰባሰብ ባለፈ ኢትዮያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርበው ከኮሚሽነሮች ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ከወረዳ ጀምሮ በምክክር ሂደቱ በስፋት የተሳተፉበት ሂደት ዜጎች የሀገር ባለቤትነታቸውን ያረጋገጡበት መኾኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ በቀጣይም በተለያዩ የዓለም ሀገራት የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረኮች በቀጣይነት ይከናወናሉ ብለዋል፡፡
“2018 ዓ.ም አበይት ስራዎች የሚሰሩበት ዓመት ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ የምክክሩ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡