የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኮሚሽኑ የኮሚሽነሮች ልዑክ ከስዊዲን አምባሳደር ጋር ተወያየ

swe

የኮሚሽኑ የኮሚሽነሮች ልዑካን በስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ዴንማርክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጋር ተወያየ
መስከረም 20/2019 ዓ.ም (ስቶክሆልም)
በስዊድንና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ውጪ ያቀናው የኮሚሽነሮች ልዑክ ስቶክሆልም በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በመገኘት በስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ዴንማርክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምሕረተአብ ሙሉጌታ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይቷል፡፡
ልዑኩ ውይይቱን ያደረገው በቅርብ ቀናት በሲዊድን ስቶክሆልም በሚካሄደው የምክክር መድረክ ዙሪያ ነው፡፡
በውይይቱ ለምክክሩ በሚያስፈልጉ የሎጂስቲክና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ስለሚከናወኑ ተግባራት ከአምባሳደሩና ባልደረቦቻቸው ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
መድረኩን ለማከናወን የተደረገውን ዝግጅት የገመገመው የውይይት መድረክ ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሲዊድንና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበት መድረክ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 24/2018 ዓ.ም ወይም ኦክቶበር 4/2025 በስቶክሆልም ከተማ የሚያካሂድ ይሆናል፡፡
https://forms.gle/SgkepyZB7icr2CVt8