የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ የምክክር ሂደት ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው

ሽ
“የኢትዮጵያ የምክክር ሂደት ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው” – የአሜሪካ የኮንግረስ አባል ስቴሴይ ፕላስኬት
መስከረም 12/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከአሜሪካ የኮንግረስ አባል ስቴሴይ ፕላስኬት ጋር ዛሬ ከሰዓት ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት ኮሚሽነሮች የኮሚሽኑን ዝርዝር ዓላማዎች እና የምክክር ሂደቱን አፈጻጸሞች በተመለከተ ለኮንግረስ አባሏ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በገለጻውም በእስካሁኑ የምክክር ሂደት የተገኙ ውጤቶችን እና ቀጣይ ዕቅዶችንም አብራርተዋል፡፡
የኮንግረስ አባሏ ስቴሴይ ፕላስኬት በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ምክክር ለዘላቂ የሰላም ግንባታ በእጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ከምክክር ውጭ ያሉ የልዩነት መፍቻ መንገዶች አውዳሚ በመሆናቸው፤ መመካከርን ባሕል ማድረግ እንደሚጠቅም መረዳታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የምክክር ሂደት ለሌሎች ሀገራትም ተሞክሮ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ተሳትፈዋል፡፡