#ENDC
መጋቢት 10/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በቀጣይ ዕቅድ ላይ ተወያዩ።
የሁለቱ ተቋማት የጋራ ኮሚቴ የእቅድ ውይይታቸውን ያካሄዱት ትላንት መጋቢት 9/2018 ዓ.ም ነው።
የኮሚቴው ሰብሳቢ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ለሀገራዊ ጉባኤው መሳካት አጋርነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተረፈ ደገቲ የቀረቡት የስራ ዕቅዶች ለሀገራዊ ጉባኤው መሳካት ወሳኝ መሆናቸውን አንስተዋል።
ምክር ቤቱ ሁሉንም ተግባራት ወስዶና የራሱን አክሎ በተሻለ ትብብር አብሮ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል።





