የትግራይ ክልል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያከናውነውን የመጀመሪያ ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የሀገራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታ መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል አስጀምሯል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) ላለፉት ጥቂት ዓመታት በትግራይ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች የተፈጠሩ ቁስሎች የሁላችንም ህመሞች ናቸው ብለዋል።
መሠረታዊ የኢትዮጵያ ችግሮች በዘላቂነት የሚፈቱት በምክክር ብቻ መሆኑን ያስገነዘቡት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ትግራይ የዚህ ሂደት አካል መሆን መጀመሯ የሚያስደስት መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም በትግራይ ክልል ምክክር ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች እስከሚፈጠሩ ድረስ ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያ ዙር ምክክር ለማድረግ ይህ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ያለ ትግራይ ተሳትፎ ምክክሩ የተሟላ እንደማይሆን አጽንኦት በመስጠትም ከባለድርሻ አካላቱ የሚገኙ ሀሳቦች ለሀገራዊ ጉባኤው ጥቅም ላይ እንደሚውሉም አስረድተዋል።
በመድረኩ ላይ ከ600 በላይ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሚዲያ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎች ተሳታዎችም በመታደም ላይ ናቸው፡፡
ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች በውይይት አዳብረው ለኮሚሽ እንደሚያስረክቡ ይጠበቃል፡፡ ሳታፊዎቹ የሀገራዊ ጉባኤ ወኪሎቻቸውንም የሚመርጡ ይሆናል፡፡
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ምክክር ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወደ ክልሉ በማቅናት እንደ ሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚያካሂድ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
https://web.facebook.com/EthioNDC





