የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የምክክር ሂደቱ ሰኬታማ እንዲሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድርሻውን ሊወጣ ይገባለ ተባለ
ነሀሴ 16/2017 ዓ/ም (ደሴ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከሴቶች ፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ጋር የሚያደርገው ሁለተኛው ዙር የውይይት መድረክ በደሴ ከተማ ተጀምሯል ፡፡
በውይይት መደረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም የምክክር ሂደቱ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሲሳተፍበትና የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም የሴቶች ተሳትፎና አዎንታዊ ሚና ለምክክሩ ስኬታማነት ድርሻው የጎላ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ለተካታታይ ሶስት ቀናት የሚደገረግ ሲሆን ከምስራቅ አማራ ዞኖች የተለያዩ ማህበራትና አደረጃጀቶችን ወክለው የተገኙ ሴቶች ፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የሚሳተፉበት ይሆናል፡፡