የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ወጣቶች ችግሮቻቸውን በምክክር ሲፈቱ ሀገርም ትውልድም አትራፊ ይሆናሉ- ከሚሽኑ

www
Published byEhiopian Ndc 57m 
ወጣቶች ችግሮቻቸውን በምክክር ሲፈቱ ሀገርም ትውልድም አትራፊ ይሆናሉ- ከሚሽኑ
ነሐሴ 9/2017ዓ.ም (ባህር ዳር)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “የወጣቶች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በአማራ ክልል ከተለያዩ አደረጃጀቶች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በባህር ዳር ከተማ እየተወያየ ነው።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህን ፤ ወጣቶች ችግሮቻቸውን በምክክር ከፈቱ ሀገርም፣ ትውልድም አትራፊ ይሆናሉ ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ የሀሳብ አለመግባባቶች ላይ በመመካከር ለሀገራችን ወቅታዊና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የወጣቶች ሚና የጎላ እንደሆነም አፅኦት ሰጥተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ባለፉት ጊዜያት አጀንዳ ባሰባሰባቸው 14 መድረኮች ወጣቶች ከአስሩን የወረዳ ማህበረሰብ መሰረቶች አንዱ ሆኖ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎችን በመለየት ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።
በተለያዩ አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶች ኮሚሽኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የምክክር ሂደቱን ሲመራና ሲያስተባብር ወጣቶችን በስፋት ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተጠቀመ አንደሚገኝ የጠቆሙት ኮሚሽር ብሌን ለዚህ ተሳትፏቸው ምስጋና አቅርበዋል።
ወጣቶች በቀጣይም በሚኖሩ የኮሚሽኑ የስራ እንቅስቃሴዎች እንደ እስካሁኑ ሁሉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለምክክሩ መሳካት ሚናቸውን እንዲወጡም ኮሚሽር ብሌን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የኮሚሽኑን የእስካሁን የስራ ሂደት የተመለከተ ገለፃ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡ ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች ከሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ጋር ነሐሴ 10 ና 11/2017 ዓ.ም በተከታታይ የሚካሄዱ ይሆናል፡፡