ወጣቶች ምክክርን ባህል ሊያደርጉ- ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም
ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (ደሴ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ከልል ወሎ ክላስተር ከሴቶች ፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደሴ ከተማ እያደረገ ያለው የውይይት መድረክ እንደቀጠለ ነው ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም ወጣቶች በጦርነት ለመሸናነፍ የሚደረገውን የማያዋጣ ባህል ትተው የምክክርን ባህል በማዳበር ሀገራችን እየገጠሟ ካሉ ችግር እንድትወጣ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል ፡፡
ኮሚሽኑ እስካሁን ለስራ በተንቀሳቀሰባቸው ክልሎች ሁሉ ወጣቶችን በስፋት እያሳተፈ እና በበጎፈቃደኝነት ጭምርም እያገለገሉት መሆኑንም ኮሚሽነር መላኩ ገልፀዋል።
በቀጣይም አጀንዳ ከመስጠት ባለፈ ሁለንትናዊ ተሳትፎ በማድረግ የምክክር ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ከወጣቶች ብዙ ይጠበቃል ሲሉም አክለዋል።
መድረኩ የተመቻቸው በቂ ግንዛቤ ባልተያዘባቸው ጉዳዮች ላይ ለወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ተመላክቷል።





