የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላትን አጀንዳዎች በይፋ ተረከበ

መጋቢት 25/2018 ዓ.ም

የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲያከናውኑ የቆዩትን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት አጠናቀዋል።

በዛሬው ዕለትም ያጠናቀሩትን አጀንዳ ለጠቅላላ ተሳታፊዎች በንባብ ካቀረቡ በኋላ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክ ኮሚሽን አስረክበዋል።

የባለድርሻ አካላቱ አጀንዳዎች፤ በርካታ ክልላዊና ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች የተካተቱባቸው ናቸው።

ከአጀንዳ ማስረከብ በተጨማሪ ለሀገራዊ ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችንም መርጠዋል።

ኮሚሽኑ አስቻይ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በትግራይ ክልል ከሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎችን ይሰበሰባል።