የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ ከጥምረት ለሴቶች ድምፅ አጀንዳዎችን ተረከበ

4d7a8553

ኮሚሽኑ ከጥምረት ለሴቶች ድምፅ አጀንዳዎችን ተረከበ
ጥር 13/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥምረት ለሴቶች ድምፅ ያሰባሰባቸውን አጀንዳዎችን በዛሬው ዕለት ተረክቧል፡፡
በርክክቡ ወቅት የተገኙት ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) የሴቶች አጀንዳዎችን ላጠናቀሩት የጥምረቱ አመራሮች በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ የደረሰበት ደረጃና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተም ዋና ኮሚሽነሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በንቃት መሳተፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥምረቱ ድጋፉን ሊቀጥል እንደሚባም በመድረኩ ተነግሯል፡፡
ጥምረቱ ያስረከባቸው አጀንዳዎች በመጀመሪያ ዙር ያልተካተቱትን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ እና አማራ ክልሎችን ያሳተፈ መሆኑን የጥምረቱ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
አሥራ ሦስት አጀንዳዎችና አራት ምክረ ሀሳቦች የተካተቱበት የአጀንዳ ሰነድ የሴቶችን የምክክር ተሳትፎና ውክልና የሚያዳብር እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ አጀንዳዎቹን በቅርቡ ለሚከናወነው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በግብአትነት እንደሚጠቀማቸውም ተገልጧል፡፡