የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ውይይት አደረገ

screenshot 20260227 162523 gallery

ኮሚሽኑ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ውይይት አደረገ

የካቲት 20/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ከመጡ እና በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ውይይቱ በክልሉ የሚደረገውን የምክክር ሂደት ለማስጀመር የተለያዩ አማራጭ ምክረ-ሀሳቦችን ለመሰብሰብ ያለመ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) የትግራይ ክልል አሁን ከገባበት ችግር ለመውጣት ሀገራዊ ምክክር ቁልፍ መሳሪያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሂደቱ የቁጥር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የተሳትፎ ጉዳይ እንደመሆኑ ያለ ትግራይ ክልል ተሳትፎ ምክክሩ ምሉዕ እንደማይሆን አፅዕኖት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ ስለ ኮሚሽኑ ዐበይት የሥራ ክንውኖች እና ቀጣይ ተግባራትም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመር ያደረጋቸውን ጥረቶች አንስተዋል።

በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንም አያይዘው በመግለፅ የመድረኩ ተሳታፊዎች ለችግሮቹ መፍትሔን እንዲፈልጉና ለሂደቱ ስኬት ኃላፊነትን እንዲጋሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሂደቱ ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ለኮሚሽነሮች ያቀረቡት የውይይቱ ተሳታፊዎች ሂደቱን የሚደግፉ ገንቢ ምክረ-ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡

ከተሳታፊዎች የቀረቡ ሀሳቦች ለምክክር ሂደቱ በግብዓትነት እንደሚውሉም በውይይቱ የተገኙ ኮሚሽነሮች ገልፀዋል፡፡