የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት ማጠናከር ያለመ መርሃግብር አካሄደ

thumb 2 copy

ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት ማጠናከር ያለመ መርሃግብር አካሄደ

ሀምሌ 26/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙሃን እና ከኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት የሚያጠናክር የውይይትና ምስጋና መርሃግብር አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) መገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት የምክክሩን ሂደት ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ለሰሩት ስራ በኮሚሽኑ ስም አመስግነዋል፡፡

በቀጣይ ሀገራዊ ምክክሩ ከመካሄዱ በፊት ሰፊ የሚድያና ኮሙኒኬሽን ስራ በመስራት በሂደቱ የላቀ የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲኖር የተለመደ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ ኮሚሽኑ በራስ አቅም እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽ ተቋማት ጋር በመተባባር የተሰራቸው ስራዎች ሪፖርት ቀርበዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት እንደተመላከተው ባላፈው አንድ አመት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ረገድ መገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ሰፊ ስራ መስራታቸው ተገልጧል፡፡

ይህ የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት የትብብር ተሳትፎ ሊቀጥል የሚችልበት ሁኔታም በቀጥይ የትብብር ገለፃ ላይ ተመላክቷል፤ መግባባት ተደርሶበታል፡፡

በዚሁ መድረክ የምክክሩን ሂደት ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ እና ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ 180 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የምስጋና ምስክር ወረቀት ከኮሚሽኑ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች፣ የህዝብና የንግድ መገናኛ ብዙሃን፣ የክልል መገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት እንዲሁም የዲጂታ፣ የሃይማኖት እና የውጪ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ናቸው፡፡

በዚህ የአጋርነት ማጠናከሪያ መድረክ ኮሚሽኑን በቅርበት የሚደግፉ ተቋማት ሃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ጨምሮ 300 የሚሆኑ እንግዶች ታድመዋል፡፡