ኮሚሽኑ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ተረከበ።
ነሀሴ 5/2017 ዓ.ም
ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናው የኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን በሀገሪቱ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ያሰባሰበበትን መድረክ ዛሬ ኦገስት 9 በሀገሪቱ መዲና ፕሪቶሪያ አካሂዷል።
መድረኩን ለማካሄድ ከተለያዩ አካላት ጋር ሲወያይ የቆየው ቡድኑ ዛሬ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረኩን አከናውኖ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች ነሀሴ 3/2017 ዓ.ምተረክቧል።
የኮሚሽኑ ልዑክ ባለፈው ሳምንት ሀምሌ 28/2017 ዓ.ም በአካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ማቅናቱ አይዘነጋም።
ኮሚሽኑ በቀጣይ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ በሲውዲንና በዱባይ ተመሳሳይ መድረኮችን በማካሄድ አጀንዳዎችን የሚሰበስብ ይሆናል።





