“ከልዩነት ይልቅ ለመግባባት ቅድሚያ መሰጠት አለበት” ምሁራን
ሰኔ 27/2017 ዓ.ም
የታሪክ ባለሙያዎች ማህበር እና የሰላምና ደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦቻቸውን ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ሥነሥርዐቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፤ ኮሚሽኑ አጀንዳ ከሚሰበስብባቸው መንገዶች አንዱ የምሑራን ጥናት ነው ብለዋል።
ተደራጅተው የቀረቡትን የምሁራን ምክረ
ሀሳቦች ለምክክር ሂደቱ እንጠቀምበታለን ሲሉም አስታውቀዋል።
የምሑራኑን የጥናት ምክረ
ሀሳብ በአስተባባሪነት የመራው ፒስ ኤንድ ላይፍ ኢንስቲትዩት ሲሆን ከሀያ ዘጠኝ ዩንቨርስቲዎች አርባ አምስት ምሑራንን ማሳተፉን በሥነሥርዓቱ ተገልጿል።
በስምንት አበይት ጉዳዮች የተደራጀው የጥናት ምክረሀሳብ፤ የልዩነት ምንጮችንና መፍትሔዎችን በተመለከተ ዝርዝር ሀሳቦች ተካተውበታል።
በሥነሥርዐቱ ላይ የጥናት የላይፍ ኤንድ ፒስ ኢኒስቲትዩት አመራሮች፣ የታሪክ ባለሙያዎች ማኅበር ተወካይ እና የሰላምና ደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ተገኝተው በሰነዱ ዙሪያ ተወያይተዋል።





