የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

እውቀትና ምርምር መር ምክክር ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ ነው- ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር)

20180408165909 4d6a2518
እውቀትና ምርምር መር ምክክር ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ ነው- ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር)
ነሀሴ 14/2017 ዓ.ም (ባህርዳር)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው ከአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ምሁራን የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
“ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው ይህ መድረክ በምክክሩ ተሳታፊ ያልሆኑ ወገኖችን ምሁራኑ በሚያቀርቡት የመፍትሄ ሀሳብ ተሳታፊ የሚሆኑበትን አማራጭ ከምሁራን ምክረ ሀሳብ ለማሰባሰብ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር)እውቀትና ምርምር መር ምክክር ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክክር ዘላቂ ሂደት ማህበረሰቡ ምክክርን ባህል እንዲያደርግ በየወቅቱ መወያየትና መመካከር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመድረኩ በውጤታማ ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ በዩኒቨርስቲ መምህራን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ በአማራ ክልል ከሚገኙ 10 ዩንቨርስቲዎች የተወጣጡ ከ200 በላይ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።