አጋር ሀገራትና ተቋማት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ
ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአጋር ሀገራት እና ተቋማት ጋር የተወያየበት መድረክ ተከናውኗል።
በመድረኩ የምክክሩን ሂደት በተመለከተ ለአጋር አካለቱ ገለጻ ተደርጓል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር) የኮሚሽኑን ስራ እየደገፉ ላሉ አጋር ሀገራትና ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይ ለሚኖሩ የምክክር ምዕራፎች የአጋር አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የታደሙ የአጋር ሀገራት ተወካዮች በሰጡት አስተያየት እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ሀገራዊ ምክክሩ ከህልምነት ወደ እውነታነት እንዲሸጋገር ያስቻሉ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተጀመሩ አበረታች ስራዎች የበለጠ ፍሬማ እንዲሆኑም የሚያደርጉትን ትብብርና ድጋፍ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡





