በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኮሚሽኑ የሉካን ቡድን ከኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር ተወያየ
ነሀሴ 2/2017 ዓ.ም
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ቡድኑ ትላንት ነሀሴ 1/2017 ዓ.ም ከኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ምክክርን መሰረት ያደረገ የልምድ ልውውጥ ተደርጓል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ሀገሪቱ ያቀናው የኮሚሽኑ ልዑክ በደቡብ አፍሪካ ቆይታው ከተለያዩ አካላት ውይይቶችን እያደረገ ነው፡፡
በነገው እለት በአካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበትን መድረክ የሚያካሂድ ይሆናል፡፡





