በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኮሚሽኑ ልዑክ ከዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ተወያየ
ሀምሌ 30/2017 ዓ.ም
በአካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናው የኮሚሽኑ ልዑክ ትላንት ከሰዓት በአካባቢው ከሚገኙ የተለያዩ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የስራ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡
ልዑኩ ትላንት በጠዋቱ መርሀግብር የመጀመሪያ ውይይቱን በሀገሪቱ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ደሊል ከድር እና ከኤምባሲው ሰራተኞች ጋር ማካሄዱ አይዘነጋም።





