የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በደቡብ አፍሪካ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የዳያሰፖራ አባላት

photo 2025 07 24 09 34 02
በደቡብ አፍሪካ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የዳያሰፖራ አባላት
ሀምሌ 17/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ የምክክር ሂደት ባለድርሻ አካል በማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ አጀንዳቸውን በመስጠት በአካል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በመሆኑም በደቡብ አፍሪካ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ ኦገስት 9/2025 ቀን በእለተ ቅዳሜ ከ8፡30 AM -5:30 PM በፕሪቶሪያ ሳውዘርን ሰን ሆቴል በሚያዘጋጀው የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ላይ እና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን በሚያስመርጥበት መርሃ-ግብር ላይ እንድትገኙ በትህትና ጋብዟችኋል፡፡
ስለሆነም በዚህ የምክክር መድረክ ላይ በግለሰብ ደረጃ ለመገኘት ከታች በተቀመጠው ሊንክ ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል የምትሏቸውን አጀንዳዎች ይዛችሁ በመገኘት በሂደቱ ላይ እንድትሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ማሳሰቢያ፡ ኮሚሽኑ በሂደቱ በየሀገራቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰቦች ማህበር፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለብቻ ጥሪ እያካሄደ ሲሆን ከላይ የተገለፀው እና በበይነመረብ ምዝገባ እንድታደርጉ የተጋበዛችሁት በመርሃ-ግብሩ ላይ በግለሰብ ደረጃ ለመሳተፍ የምትፈልጉትን ብቻ እንደሆነ እናሳስባለን፡፡