በካናዳ ለምትኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዳያሰፖራ አባላት
ነሀሴ 20/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ የምክክር ሂደት ባለድርሻ አካል በማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ አጀንዳቸውን በመስጠት በአካል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በመሆኑም በካናዳ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ ከሰፕቴምበር 6/2025 ጀምሮ በካናዳ ቶሮንቶ በሚያዘጋጀው የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ላይ እና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን በሚያስመርጥበት መርሃ-ግብር ላይ እንድትገኙ በትህትና ጋብዟችኋል፡፡
ስለሆነም በዚህ የምክክር መድረክ ላይ በግለሰብ ደረጃ ለመገኘት ከታች በተቀመጠው ሊንክ ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል የምትሏቸውን አጀንዳዎች ይዛችሁ በመገኘት በሂደቱ ላይ እንድትሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ኮሚሽኑ በሂደቱ በየሀገራቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰቦች ማህበር፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለብቻ ጥሪ እያካሄደ ሲሆን ከላይ የተገለፀው እና በበይነመረብ ምዝገባ እንድታደርጉ የተጋበዛችሁት በመርሃ-ግብሩ ላይ በግለሰብ ደረጃ ለመሳተፍ የምትፈልጉትን ብቻ እንደሆነ እናሳስባለን፡፡ የስብሰባውን ቦታ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
https://forms.gle/y1kwixvgRVbdGiK99





