በአፍሪካ አህጉር ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ በሙሉ
በዙም በሚደረግ ውይይት
ሃምሌ 17/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ የምክክር ሂደት ባለድርሻ አካል በማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ አጀንዳቸውን በመስጠት በዙም በሚደረግ ውይይት ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በመሆኑም በአፍሪካ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ ጁላይ 31/2025 ቀን በእለተ ሀሙስ ከሰዓት በሃላ 3፡00PM-6:00PM በሚያዘጋጀው የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ መርሃ-ግብር ላይ እንድትገኙ በትህትና ተጋብዟችኋል፡፡
ስለሆነም በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ለመገኘት ከታች በተቀመጠው ሊንክ ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል የምትሏቸውን አጀንዳዎች ይዛችሁ በመገኘት በሂደቱ ላይ እንድትሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡





