በአዲስ አበባ ከተማ ለምትኖሩ የትግራይ ተወላጆች የቀረበ የምክክር ተሳትፎ ጥሪ
መጋቢት 15/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልልን የምክክር ሂደት በትግራይ ክልል ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ሲፈጠር በሌሎቹ የአገራችን አካባቢዎች ያከናወናቸውን ተግባራት የሚያከናውን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ እንዲሁም ከትግራይ ክልል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የሚመጡ ወኪሎችን በማሳተፍ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረኩንና የሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታን በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አቅዷል፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን መድረክ ከመጋቢት 23/2018 ዓ.ም እስከ 25/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል የሚያካሂድ ይሆናል፡፡
ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል ሁሉም ዞኖች ለሚሳተፉ የወረዳ ሕብረተሰብ ክፍሎች፣ የመንግሰት አካላት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የበጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች በደብዳቤ ጥሪ የሚያደርግ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
በተጨማሪም በዚህ የምክክር ሂደት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውን እና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ለማሳተፍ ኮሚሽኑ በበይነ-መረብ አማካኝነት ምዝገባ ያካሂዳል፡፡
በመሆኑም በዚህ የምክክር ሂደት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ በአዲስ አበባ ከተማ የምትኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ እንድትመዘገቡ ኮሚሽኑ እየጋበዘ በምዝገባ ወቅት በምታስቀምጡት የስልክ ቁጥር ጥሪ እንደሚተላልፍላችሁ ኮሚሽኑ በአክብሮት ይገልፃል፡፡
https://forms.gle/2kYQFqcmVsekKKJi7





