የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ አጀንዳዎችን ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች በርካታ ናቸው- ኮሚሽኑ

photo 2025 08 22 06 05 18 (3)

በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ አጀንዳዎችን ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች በርካታ ናቸው- ኮሚሽኑ

ነሀሴ 16/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ዲያስፖራውን በምክክር ሂደቱ ለማሳተፍ በወጣው መርሀግብር መሰረት በቅርቡ በአሜሪካ እና በካናዳ የአጀንዳ ማሰባሳብና የተወካዮች ምርጫ ተግባራትን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀው ስምሪት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የሰሜን አሜሪካ የምክክር መድረክ ኦገስት 30 ወይም ነሀሴ 24/2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የጠቆሙት ቃል አቀባዩ በዚህ መድረክ በመሳተፍ በመደማመጥና በመከባባር ተመካክረው አጀንዳዎችን ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች እየተመዘገቡ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በበይነ መረብና በአካል እንዲሁም ኮሚሽኑ ባቀረበላቸው የመመዝገቢያ አማራጮች በመመዝገብ መሳተፍ እንደምችሉ ተገልጧል፡፡

መድረኮቹ ከሚካሄድባቸው ከተሞች ወይም ግዛቶች ውጭ ያሉና በመድረኩ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ መሳተፍ እንደሚችሉም አቶ ጥበቡ ጠቁመዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የምክክር ሂደቱን ይበልጥ አካታችና አሳታፊ ለማድረግ በህግ ጥላ ሥር የሚገኙ ዜጎችን ሀሳብ ለማካተት ኮሚሽኑ አስቻይ ሁኔታዎች መፍጠሩን አስገንዝቧል።

የኮሚሽኑን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ፍትህ ሚኒስቴርና የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ባደረጉት ውይይት ታራሚዎችና የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታታሉ ያሉ ዜጎች በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ የሚያስችል በጎ ምላሽ መስጠታቸውን አቶ ጥበቡ ተናግረዋል።

እነማን በምን አግባብ ይሳተፋሉ ለሚለውም ኮሚሽኑ ቴክንካል ስራዎችን እየሰራ መሆኑን  ገልፀው፤ ለተግባራዊነቱ ከፈደራል ማረሚያ ቤቶች ጋር እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ከዚህ የሚገኘውን ተሞክሮ በማስፋት በክልሎች የሚገኙ ታራሚዎችንም ለማሳተፍ የሚያስችሉ ሥራዎች ይሰራሉ ሲሉም ገልፀዋል፡፡