የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በምክክር ሰላምን ለማረጋገጥ ሴቶችን፣ ወጣቶችንና አካል ጉዳተኞችን በንቃት ማሳተፍ ይገባል” ኮሚሽኑ

img 20251004 154356 273

በምክክር ሰላምን ለማረጋገጥ ሴቶችን፣ ወጣቶችንና አካል ጉዳተኞችን በንቃት ማሳተፍ ይገባል” ኮሚሽኑ

መስከረም 24/2018

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ሚና ለሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሱማሌ፣ በቤኒሻጉል ጉምዝና እና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር የውይይት መድረኮች እያከናወነ ነው።

በመድረኮቹ ላይዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ(ፕሮፌሰር)፣ ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድኅን፣ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በንግግራቸውም ኮሚሽኑ አጀንዳ ባሰባሰባቸው የምክክር ምዕራፎች ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች በንቃት መሳተፋቸውን አስታውሰው እነዚህ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

በውይይት መርሀግብሮቹ ላይ ስለ ምክክር ምንነት፣ አስፈላጊነትና የባለድርሻ አካላት ሚናን በተመለከተ መነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ከሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች አደረጃጀቶች ከተወጣጡ ተሳታፊዎች ጋር እየተደረገ ያለው ይህ የምክክር መድረክ ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያደረገ ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክርበት ተግባር አንዱ አካል ነው፡፡

ወጣቶች፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ኢትዮጵያ የጀመረችው የምክክር ሂደት ተሳክቶ የሚፈለገው ውጤት እንዲገኝ ትልቅ ኃላፊነት እንዳላበቸው አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ኮሚሽኑ ተመሳሳይ መድረክ በአማራ ክልል ደሴና ባህርዳር ክላስተር ማካሄዱ ይታወሳል፡፡