የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በምክክር ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ፤ የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ሚና አላቸው- ኮሚሽኑ
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሃይማኖት ተቋማት ምሁራን ጋር በዛሬው ዕለት የውይይት መርሐግብር አከናውኗል፡፡
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ በዚህ መድረክ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ያሉ ቤተ-እምነቶች ያዳበሩት ማህበረሰቡን የማስተሳሰር እሴት ለሀገራዊ መግባባት መሠረት ነው፡፡
ኮሚሽኑ ቤተ-እምነቶችን በምክክሩ ሂደት ላይ በስፋት እያሳተፈ ያለው የማይተካ ሀገራዊ አስተዋጽኦ ስላላቸው እንደሆነም ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ገልጸዋል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር በበኩላቸው በነፃነትና በክብር እንድንኖር የሃይማኖት ተቋማት ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር እጅግ መሠረታዊ እና ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያሉንን አለመግባባቶች በሠለጠነ መንገድ ለመፍታት የምክክር ሂደት እየተከናወነ መሆኑንም ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ተናግረዋል፡፡
አክለውም የሃይማኖት ተቋማት፤ሀገር እየመከረች መሆኗን ከግንዛቤ በማስገባት ሚናቸውን አልቀው የሚወጡበት ታሪካዊ አጋጣሚ ላይ አንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት የሃማኖት ምሁራን የሰላም ትርክትን በመፍጠር ለሀገራዊ መግባባት ብዙ ኃላፊነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን የመነጋገር ባሕልን እንዲያዳብሩ ሃይማኖቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ኮሚሽነር አምባዬ አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ ኮሚሽኑ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ የታቀዱ ሥራዎችን በተመለከተ ገለፃ ቀርቦ ተሳታፊዎች ተወያይተውበታል፡፡
+6
See insights

Create ad
All reactions:

You and 162 others