ስዊድን ስኮትሆልም የሚገኘው የኮሚሽነሮች ልዑክ ይፋዊ የስራ ጉብኝቱን አጠናክሮ ቀጥሏል
መስከረም 23/2017 ዓ.ም (ስኮትሆልም)
በአካባቢው ከሚገኙ ሀገራት አጀንዳ ለማሰባሰብና የሀገራዊ ምክክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን ለመምረጥ ስዊድን ስቶክሆልም የሚገኘው የኮሚሽነሮች ልዑካን ቡድን ከተለያዩ አካላት ጋር እየተወያየ ነው፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ትላንት መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ከስቶክሆልም ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ከከተማዋ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ጋር ተወያይተዋል፡፡
አባላቱ ከOlof Palme International Center እና ከስዊድን የሰላም ኢንስቲትዩት (Folke Bernadotte Academy) የሥራ ኃላፊዎች ጋርም በመገናኘት ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቶቹ ላይ የተገኙት ኮሚሽነሮች ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውንና በቀጣይ ለማከናወን ያቀዳቸውን ዐበይት ተግባራት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
የዓለምአቀፍ አጋሮች ድጋፍ ለምክክር ሂደቱ ውጤታማነት የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡
ስዊድን የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት በሂደቱ ላይ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱም ነው የተገለፀው፡፡
ከኮሚሽነሮቹ ጋር የተወያዩት እነዚህ የሲዊዲን ተቋማት ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ምክክር እንደሚደግፉ ለኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን አባላት አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነገ ቅዳሜ መስከረም 24/2017 ወይም ኦክቶበር 4/2025 በሲዊዲን፣ በኖርዲክ ሀገራት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዳያሰፖራ አባላት አጀንዳ የሚሰባስብበትና ሀገራዊ ምክክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን የሚመርጥበት መድረክ በስቶክሆልም ከተማ ያካሂዳል፡፡





