የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የመሳተፋቸው አስፈላጊነት
ሀምሌ 21/2017 ዓ.ም
በሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊ በመሆኑ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን የሀሳብ ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች እንደ ምክክር ባሉ ሰላማዊ አማራጮች ከመፍታት ይልቅ የሀይል አማራጮች ጥቅም ላይ ሲውሉ ይታያል፡፡
ግጭቶች ከፍ ሲልም ጦርነቶች ሲፈጠሩም ሴቶች ግንባር ቀደም ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረጉ ሂደቶች ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ሀገራዊ ምክክር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ እንደመሆኑ ስርዓተ-ጾታ ትርጉም ያለው አካታችነትን፣ ፍትሀዊነትንና እኩልነትን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
ሴቶች በምክክር ሂደቶች ውስጥ ሙሉና ትርጉም ያለው ተሳትፎን በማድረግ ወቅታዊና ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮቻችንን በጋራ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፤
ምክክር ከቤት ውስጥ ተጀምሮ በሂደት እየጎለበተ የሚሄድ ባህል እንደመሆኑ ሴቶች በእናትነት ብሎም በእህትነት በተግሳፅ እና በፍቅር ቤተሰባቸውን በማነፅ ለችግሮች በቤት ውስጥ መፍትሔ መፈለግን ያስተምራሉ፡፡
ይህም ሴቶችን የሀገራዊ ምክክሩ ዋነኛ ከዋኞች እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው መሆኑ፤
ሴቶች የማህበረሰቡ ግማሽ አካል በመሆናቸው እና በሌሎች ምክንያቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች መሳተፋቸው እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!