የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ምክንያታዊነት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እንዴት እየተቃኘ ነው?

gra

ምክንያታዊነት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እንዴት እየተቃኘ ነው?
መስከረም 19/2017 ዓ.ም
ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተቋቋመበት የመመስረቻ አዋጅ ላይ ምክንያታዊነት ከሀገራዊ ምክክሩ መርሆዎች አንዱ ተደርጎ መደንገጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ፅንሰ-ሀሳቡ በምክክር ሂደት ውስጥ በምን አግባብ ጥቅም ላይ እንደሚውል ማወቁ አስፈላጊ ነው፡፡
በሀገራዊ ምክክር አውድ ውስጥ ምክንያታዊነት ከስሜታዊነት፣ ከጥላቻ እና ከሀሳብ ግትርነት የፀዳ በአንፃሩ አመክንዮን እና ማስረጃን መሰረት ያደረገ ውይይትን እና ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያግዝ የስነ-ምግባር መርህ ነው፡፡ ይህም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የጋራ መፍትሔን ለመፈለግ የሚያደርጉትን በጎ ጥረት ያጠናክራል፡፡
ይህንን መነሻ በማድረግ ምክንያታዊነት በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ እንዴት ተፈፃሚ እንደሚሆን የሚከተሉት ሀሳቦች ያብራራሉ፡፡
1. አመክንዮን እና ማስረጃን መሰረት በማድረግ
በዚህ ሂደት ዜጎች እና ባለድርሻ አካላት ከስሜታዊነት እና ጥላቻ በፀዳ አኳኋን በውይይቶች ላይ ተሳትፎን እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ገለልተኝነትን እና ፍትሀዊነትን መሰረት በማድረግ
ምክንያታዊ በሆነ የሀገራዊ ምክክር ሂደት ሚዛናዊ የሆኑ ውይይቶች እንዲደረጉ ከማገዙም በላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድምፆቻቸው በእኩልነት እንዲሰሙ በር ከፋች ነው፡፡
3. በሰው ልጆች እኩልነት ማመንን በማበረታታት
በሀገራችን የሚደረጉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የሰው ልጆች በጋራ ችግሮቻቸው ላይ የሚወያዮባቸው እንደመሆናቸው መጠን የሰው ልጀችን እኩልነት እና ተፈጥቶአዊ ማንነት ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
ሀገራዊ ምከክር ለሀገራዊ መግባባት!