ለምክክሩ መሳካት የሚጠበቅብንን ድጋፍ እናደርጋለን- በሲዊዲን የሚገኙ የኢትዮጵያዊያ ዳያስፖራ አባላት
መስከረም 17/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሲዊዲን እና አካባቢው ሀገራት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ትላንት መስከረም 16/2017 ዓ.ም ምሽት በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር)ኮሚሽኑ በእስካሁን የስራ ሂደቱ ያከናወናቸውን ተግባራትና የቀጣይ ትኩረቶቹን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ተሳታፊዎች በኮሚሽኑ አሰራርና በምክክሩ ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆኑላቸውን ጉዳዮች በጥያቄና አስተያየት መልክ አንስተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ምክክር እንዲሳካ ምኞታቸው መሆኑን የገለፁት በሲዊድንና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለስኬቱ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሲዊድንና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውለደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበት መድረክ መስከረም 24/2018 ዓ.ም ወይም ኦክቶበር 4/2025 በስቶኮልም ከተማ የሚያካሂድ ይሆናል፡፡





