ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተለዩ አጀንዳዎች በምን መስፈርት ተመረጡ? በኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር)
ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳዎችን ለሃይማኖት ተቋማትና ለሲቪክ ማኅበራት አቅርቦ ግብዓት አሰባስቧል።
ዛሬ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም በተካሄደው መድረክ ላይ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳዎች የተቀረፁበትን መሥፈርት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) አቅርበዋል።
እንደ ኮሚሽነር አምባዬ ማብራሪያ መስፈርቶቹ የሚከተሉት ናቸው
👉 የጉዳዩ ጭብጥ የህገመንግስት ማሻሻልን የሚያስከትል ከሆነ
👉ጉዳዩ በሀገሪቱ ያሉ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ የአለመግባባት መንስኤዎችን እና ችግሮችን በትክልል የሚዳስስ እና በጉዳዩ ላይ መመካከር ችግሩን በትክክል የሚፈታ ሆኖ ሲገኝ፡፡
👉ጉዳዩ ላይ ምክክር ቢደረግበት በህዝብ እና በሕዝብ መካከል ያሉትን ግንኙነቶች በማሻሻል መተማመንን የሚፈጥር ሆኖ ሲገኝ፡፡
👉አዲስ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር የሚረዳ ጉዳይ ሆኖ ሲገኝ
👉ጉዳዩ ላይ ምክክር ቢደረግበት በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያሉትን ግንኙነቶች በማሻሻል መተማመንን የሚፈጥር ሆኖ ሲገኝ፡፡
👉የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ ለማስቻል አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን፡፡
👉ቅቡልነት ያለው ሀገረ-መንግስት በመገንባት ሂደት ጠንካራ መሰረት ለመጣል የሚያግዝ ሆኖ ሲገኝ፡፡
👉የሰላም ግንባታ፡- ወቅታዊ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መንገድ በመፍታት አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር የሚያግዝ ሆኖ ሲገኝ፡፡
👉ለሀገራዊ መግባባት አስተዋጽ የሚያደርግ ሲሆን፡፡
👉የተሸረሸሩ ሀገራዊ እሴቶችን ለማደስ አስተዋጽዖ የሚያደርግ ሲሆን፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!




