የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ለሀገራዊ ምክክር ሂደት የአካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው

akal
ለሀገራዊ ምክክር ሂደት የአካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው
ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም(ባህርዳር)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከተለያዩ አጀረጃጀቶች ከተወጣጡ አካል ጉዳተኞች ጋር በባህር ዳር ከተማ ተወያይቷል።
“የአካል ጉዳተኞች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የአካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህን አስገንዝበዋል።
በኮሚሽኑ የእስካሁን የምክክር ሂደት ላይ አካል ጉዳተኞች በተለያየ መልኩ በንቃት ሲሳተፉ እንደነበር ኮሚሽነር ብሌን አስታውሰዋል።
በቀጣይ የኮሚሽኑ ስራዎችም ትርጉም ባለው መልኩ ተሳትፎአቸውን እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሯ ጥሪ አቅርበዋል።
በምክክር መድረኩ የኮሚሽኑ የእስካሁን የስራ ሂደት፣ የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎና ውክልናን በተመለከተ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች ነሐሴ 9 እና 10/2017 ዓ.ም ከወጣቶች እና ሴቶች ጋር መደረጉ ይታወሳል።