ሁላችንንም ያሳተፈ ምክክር እየተካሄደ ነው- ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህን
ሰኔ 18/2017 ዓ.ም (ደሴ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ወሎ ክላስተር ከሰኔ 16/2017 ዓ.ም ጀምሮ በደሴ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው ፡፡
በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ዞኖች የተወጣጡ ወጣቶች፤ ሴቶችና የአካል ጉዳተኛ በመሳተፍ ላይ ናቸው ፡፡
በዛሬው እለት ከአካል ጉዳተኞች ጋር እየተደረገ ባለው ውይይት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብሌን ገብረ መድህን የምክክር ሂደቱ ለአካል ጉዳተኞች ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ኮሚሽኑ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል ፡፡
በኮሚሽኑ አሰራር ስነ ስርአት መሰረት አካል ጉዳተኞች እንደ አንድ የማህበረሰብ ክፍል ከመወከላቸው በተጨማር በሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም በወጣቶች ፣በሴቶች ፣ በመምህራን፣ በመንግስት ሰራተኞች ወዘተ ውስጥም አካል ጉዳተኞች ተወክለው እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ኮሚሽነር ብሌን አክለውም ኮሚሽኑ ሁላችንም የሚመስል፤ሁላችንም የሚወክል፤ ኮሚሽን በመሆኑ ምክክር እያካሄደ ነው ብለዋል።
አካል ጉዳተኞ የማህበረሰብ ክፍሎች ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት የበኩላችሁን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።





